Make your own free website on Tripod.com
Home
Appostolic Gate

      እግዚአብሔር አምላክ ነው። በአምላክነቱም ፈቃድ የሰራው ዘለአለማዊ እቅድ አለው።
እቅዱም በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለው ሐሳቡ በሰማይም በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ስር ለመጠቅለል ነው።

        ለዚህ ክቡር ስራ ደግሞ ልጁን ለመስቀል ሞት አሳለፎ በመስጠት አረጋገጠ። እንዲሁም ክርስቶስ ከሙታን በማስነሳት በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ በማስቀመጥ ከግዛት፣ ከስልጣናት፣ ከሐይላት፣ በአሁኑ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚቻለው ስም ሁሉ በላይ እዲሆን አድርጎታል። እግዚአብሔር ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዛለት። በቤተክርስትያንም በማንኛውም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾሞታል። ስለዚህ ይህንን የእግዚአብሔር እቅድ በመረዳትና ቅዱሱ መንፈስ ከገለጠልን ከቃሉ ሚስጢር በመከተል የምንሰራ ነን።


በነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅር
የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ጸጋ
የመንፈስ ቅዱስ ህብርት ከመንፈሳቹሁ ጋር ይሁን! አሜን!

አገልጋይ ረዳኢ ታደለ::